የፕሮግራም አጋሮች

“ሕልሜ የማሕፀን ፊስቱላን ከኢትዮጵያ ማጥፋት ነው። በሕይወት ዘመኔ ይሄን አላሳካ ይሆናል። እናንተ ግን ትችላላችሁ።”

– ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን

ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ፕሮግራሞችን የበለጠ ለማሳደግ እና ለማጠናከር ከተለያዩ አጋሮች ጋር በትብብር ይሠራል። የአጋርነት ትብብሮች የተሻሉ ተግባራትን ለማከናወን እና አቅርቦቶችን ለማሻሻልያግዛሉ፣ ይህም ለኢትዮጵያ ሴቶች በተቻለ መጠን የተሻለውን የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ይረዳል።

ግሪንላምፕ


የሶላር ሻንጣ ኢኒሼቲቭ 

ከ2012 ጀምሮ ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከግሪን ላምፕ ጋር በመተባበር በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሴቶችን ጤና ለማሻሻል እየሠራ ነው። ግሪን ላምፕ የሶላር ሻንጣ ኢኒሼቲቭ ብዙ ጊዜ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እና ብርሃን ለሌላቸው የሃምሊን የገጠር አዋላጅ ክሊኒኮች ዘላቂ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል።

ግሪንላምፕ ምሩቅ የሃምሊን አዋላጆች በተሰማሩባቸው የገጠር ጤና ማዕከላት ከፀሐይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መሣሪያዎችን ይገጥምላቸዋል።፣ ይህም ለቀዶ ሕክምና ጥራት ያለው መብራት እና ለአደጋ ጊዜ ወደ ሪፈራል ለመላክ እንዲቻል የሞባይል ስልኮችን ኃይል ለመሙላት፣ ለፅንስ ​​ዶፕለር እና አስፈላጊ መድኃኒቶችን እና ክትባቶችን በማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይልን ይሰጣል። በዚህም አዋላጆቻችንን ደኅንነቱ የተጠበቀ የማዋለድ አገልግሎትን እንዲሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻችላቸዋል።  በተለይም ለእናቶች ሞት ግንባር ቀደም መንሥዔ የሆነውን የድኅረ ወሊድ ደም መፍሰስን – በማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጥ ባለበት ኦክሲቶሲን ተጠቅሞ ለመከላከል ያስችላል።

የግሪን ላምፕ የሶላር ሻንጣዎች አሰቃቂ የወሊድ ጉዳቶች እና ሊወገድ የሚችል ሞትን በመቀነስ ደኅንነቱ የተጠበቀ ወሊድን እንዲኖር ያስችላሉ፤ ሴቶችም ወደ ጤና ማዕከላት እንዲመጡ ያበረታታሉ። ግሪን ላምፕ እስካሁን ድረስ የሃምሊን ማዋለጃ ክሊኒኮችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ250 በላይ የሶላር ሻንጣዎችን በመግጠም እና በመጠገን ከ1 በላይ በመውለድ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶችን መድረስ ችሏል። እዚህ ላይ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ

የሃምሊንአዋላጆች የቀድሞተማሪዎችኔትወርክ

ግሪን ላምፕ እ.ኤ.አ. በ2018 ለሃምሊን የአዋላጆች ኮሌጅ ተመራቂዎች ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ሥልጠና የሚሰጥ የሃምሊን አዋላጆች የቀድሞ ተማሪዎች ኔትወርክን አቋቋመ።

የኔትዎርኩ ግቦች የአመራር እና ሙያዊ ዕድገት ማምጣትን፣ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ምርጥ ሥራን ማስፋፋት፣ እንዲሁም በፕሮጀክቶች፣ በመሣሪያዎች እና በክኅሎት ሥልጠናዎች ላይ ከአዋላጆች የሚሰጡትን አስተያየቶች ማመቻቸትን ያጠቃልላሉ።

የኔትወርኩ አባላት ዓመቱን ሙሉ በበይነ መረብ ኦንላይን፣ ለመሰባሰብ፣ ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም በአዋላጅነት ላይ ያሉ አዲስ ክኅሎቶች እና መሻሻሎችን ለመቀያየር ምቹ በሆኑ ክልላዊ እና ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ ይገናኛሉ። እያንዳንዱ ክልል ኔትወርኩ እንዴት እንደሚመሠረት እና እንደሚያስተዳድር ይወስናል። በአዋላጆች መካከል ግንኙነትን ለማስተዳደር እና ለማስተባበር የክልል ተወካዮች በየአካባቢው ይመረጣሉ።

«የሃምሊን አዋላጆች የቀድሞ ተማሪዎች ኔትወርክንለማነሳሳት እና ለመደገፍ ከግሪን ላምፕ ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ አዋላጆች እንደ ተቆርቋሪ እና ችሎታ ያላቸው አዋላጆች ሆነው በሙያቸው ንቁ ሆነው እንዲቀጥሉ፣ በአገር ውስጥ በወሊድ አገልግሎት ላይ ማሻሻያዎችን እንዲመሩ እና ለሴቶች እና ልጃገረዶች አርአያ ሆነው እንዲሠሩ ማበረታቻ መስጠት ነው።  በገጠር ማኅበረሰቦች ውስጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ወሊድ ቁጥርን ለማሻሻል ፍጹም ቁልፍ ናቸው ብለን እናምናለን። በመስክ ላይ የበለጠ ድጋፍ በተደረገላቸው መጠን የሚሠሩት የመከላከል ሥራ ውሎ አድሮ ፊስቱላን የማጥፋት ዕድሉ ሰፊ ነው።»

ክሪስቲና ብሌቸር፣ የግሪን ላምፕ ፕሬዝዳንት

ለሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የምሩቃን ኔትወርክ መመሥረቱ በሃምሊን አዋጆች ኮሌጅ የተገኘውን የትምህርት ጥራት ለማስቀጠል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። በመሠረቱ ኔትወርኩ ለሃምሊን አዋላጆች ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ሥልጠና በመስጠት አዋላጆችን የበለጠ የተሸሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል!

  
«የሃምሊን አዋላጆች የቀድሞ ተማሪዎች ኔትወርክንለማነሳሳት እና ለመደገፍ ከግሪን ላምፕ ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ አዋላጆች እንደ ተቆርቋሪ እና ችሎታ ያላቸው አዋላጆች ሆነው በሙያቸው ንቁ ሆነው እንዲቀጥሉ፣ በአገር ውስጥ በወሊድ አገልግሎት ላይ ማሻሻያዎችን እንዲመሩ እና ለሴቶች እና ልጃገረዶች አርአያ ሆነው እንዲሠሩ ማበረታቻ መስጠት ነው።  በገጠር ማኅበረሰቦች ውስጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ወሊድ ቁጥርን ለማሻሻል ፍጹም ቁልፍ ናቸው ብለን እናምናለን። በመስክ ላይ የበለጠ ድጋፍ በተደረገላቸው መጠን የሚሠሩት የመከላከል ሥራ ውሎ አድሮ ፊስቱላን የማጥፋት ዕድሉ ሰፊ ነው።»

ክሪስቲና ብሌቸር፣ የግሪን ላምፕ ፕሬዝዳንት

ዩኤንኤፍፒኤ ኢትዮጵያ


ታካሚዎችን መለየትና ሴቶችን ከሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ጋር ማገናኘት  

እ.ኤ.አ. በ2020 ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ እና ዩኤንኤፍፒኤ ኢትዮጵያ ያልታከመ የማሕፀን ፊስቱላ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን የእናቶች ጤና ውጤቶችን ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶችን ለማጣመር አጋርነት መሠረቱ።

ይህ የሦስት ዓመት የጋራ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያን ሴቶች የፊስቱላ እና የማሕፀን/የፊኛ/የዓይነምድር ከረጢት ወደ ውጭ መውጣት ችግር (ፊስቱላ) ሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ እንዲሁም በማሕፀን በር ካንሰር ምርመራ እና ሪፈራል ብዙ ሴቶችን መድረስ ላይ ያተኮረ ነው።

ፕሮጀክቱበወሊድላይጉዳትለደረሰባቸውሴቶችጥራትያለውአገልግሎትተደራሽነትበማሻሻልላይያተኩራል።ፕሮጀክቱእ.አ.አ. ሴፕቴምበር 2019 ከተጀመረበትጊዜጀምሮ 996 ሴቶችተለይተውታክመዋል።

«ይህ ፕሮጀክት ለእኛ ትልቅ ትርጉም አለው። ታካሚዎቻችንን እንዴት መንከባከብ እና ማከም እንዳለብን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ ነገር ግን ባለፉት ዓመታት እነሱን መለየት ትልቅ ፈተና ሆኖብን ቆይቷል። በዚህ ፕሮጀክት ታካሚዎችን በትብብር የመለየት ሥራ በመሥራት በመላ አገሪቱ ሕክምና ያላገኙ ሴቶችን መድረስ እና የማሕፀን ፊስቱላ በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ችግር እንዳይሆን የማድረግ ዓላማችንን ማሳካት እንችላለን።»

ተስፋዬ ማሞ ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ውሜንስ ሆፕ ዓለም አቀፍ 


በሃምሊን ደስታ መንደር ሴችን የማብቃት ፕሮግራም 

እ.ኤ.አ. በ 2021 የሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የደስታ መንደር ቡድን ከውሜንስ ሆፕ ዓለም አቀፍ ጋር በመተባበር (የሃምሊን ማገገሚያ እና የመልሶ ማቋቋም ማዕከል) የገቢ ማስገኛ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የቀድሞ ታካሚዎች ሴቶችን የማብቃት ፕሮግራም የተሰኘ አዲስ የሙያ ሥልጠና  ጀምሯል።

ሴቶችን የማብቃት ፕሮግራም በደስታ መንደር ለሦስት ወራት የሚቆይ የመኖሪያ ፕሮግራም ሲሆን በጣም ለሚያስፈልጋቸው ሴቶች ተግባራዊ የሆነ የሙያ ክኅሎት ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህ እጅግ አስደናቂ ተነሳሽነት በውሜንስ ሆፕ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ሴቶችን በወሳኝ የሙያ ክኅሎት፣ የአነስተኛ ንግድ መመሪያ እና የአመራር ሥልጠናዎች ይሰጣል።

የሙያ ሥልጠና መርሐ ግብሮቹ የምግብ አቅርቦትና ምግብማቀነባበር፣ የአትክልትና የዶሮ እርባታ፣ የንብ ማነብ እና የሸክላ ሥራን ያካትታሉ። የሙያ ሥልጠናው ጥራትና ስፋት በተሻሻለ የታካሚዎች ልየታ፣ አዲስ የሥልጠና መመሪያዎች እና የሥልጠና ተቋማት ድጋፍ መሻሻሉን ቀጥሏል። በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉ ሠልጣኞች የበለጠ የገቢ ማግኛ ነጻነት እና ምርጫዎች ያሉት ብሩህ የወደፊት ጊዜ ለመፍጠር አቅም አጎልብተዋል።

የቀድሞ ታካሚዎች የሰጡት አስተያየት እጅግ በጣም አወንታዊ ነበር። ፕሮግራሙ እንደ ሙሉ ላሉ ብዙ ሴቶች ሕይወት ቀያሪ  ነው። «በብዙ ስቃይ ውስጥ ነበር የምኖረው። ከዳንኩ በኋላ ወደዚህ ሥልጠና ስንጋበዝ በጣም ደስተኛ ነበርኩ እና የምገልጽበት ቃላት አጥቼ ነበር… በመንደሬ ትንሽ ምግብ ቤት ከፍቼ ምግብ ለመሸጥ እመኛለሁ።»

የሴቶች ማብቃት ፕሮግራሙ ባለፈው ዓመት 215 ሴቶችን አሠልጥኗል። እስካሁን 425 ሴቶች በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ሲሆኑ በ2023 ተጨማሪ 240 ሴቶች ይሠለጥናሉ።

የክልል ጤና ቢሮዎች 


የሃምሊን የአዋላጅነት ማስተርስ ምልመላ 

የሃምሊን አዋላጅ ነርሶች ኮሌጅ በቅርቡ በክሊኒካል ሚድዋይፍሪ የድኅረ ምረቃ ሳይንስ ትምህርት ክፍል የከፈተ ሲሆን የመጀመርያዎቹ 31 ተማሪዎች እ.አ.አ. በጃንዋሪ 2022 ትምህርታቸውን ጀምረዋል። ከኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋላጅነት በቢኤስሲ የተመረቁ ተማሪዎች በሙሉ ለፕሮግራሙ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ። መርሐግብሩ በወሊድ ክትትል፣ የማሕፀን ሕክምና እና አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ክብካቤ ላይ ያተኩራል።

ይህ ሁለት ዓመት ተኩል የሚፈጀው የማስተርስ መርሐ ግብር በሃምሊን አዋላጅ ክሊኒኮች በኢትዮጵያ ሩቅ አካባቢዎች የሚካሄዱ የ582 ሰዓታት የተግባር ትምህርቶችን ያካትታል። የማስተርስ ተመራቂዎቹ በቀዶ ሕክምና ማዋለድ እና የተወሳሰቡ ወሊዶችን በመቆጣጠር የተካኑ ይሆናሉ። ቀጣዮቹ የአዋላጅ ነርስነት አስተማሪዎችም ይሆናሉ።

ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በዚህ ፕሮግራም የተሻለ ጥራት ያላቸው ተወዳዳሪዎች እንዲመጡ ለማስቻል ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር አጋርነት ፈጥሯል። የክልል ጤና ቢሮዎች ከመግቢያ መስፈርት አንጻር በትምህርት ግምገማ ላይ ተመርኩዘው ለፕሮግራሙ ዕጩዎችን ያቀርባሉ።

ለአዲሱ ማስተር ኘሮግራም የሚያመለክቱ የሃምሊን ቢኤስሲ አዋላጅ ምሩቃንን ለመደገፍ  ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ እና የክልል ጤና ቢሮዎች ለቀድሞ የሃምሊን ኮሌጅ አዋላጅ ምሩቃን 50% ቦታ ለመስጠት ተስማምተዋል። በክልል ጤና ቢሮዎች የተመረጡ ሁሉም የቀድሞ የሃምሊን ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ አጋሮቻችን የገንዘብ ድጋፍ ይከታተላሉ።

የሃምሊን ኮሌጅ ዓላማ ፕሮግራሙን ማሳደግ እና ወደፊት የሚቀበላቸውን ተማሪዎች ቁጥር በየዓመቱ መጨመር ነው። ሌላ የ30 ተማሪዎች ቅበላ እ.አ.አ. በጃንዋሪ 2023 ይጀምራል። ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ የቀድሞ የሃምሊን ቢኤስሲ ተመራቂዎች ናቸው።