ፕሬስ ሪሊዝ

መጋቢት 10፣2012 ዓ.ም.

የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መስራች ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው አረፉ

የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መስራች የሆኑት ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ትላንት ሌሊት ረቡዕ መጋቢት 9 ቀን በ 96 ዓመታቸው አረፉ፡፡ ዶ/ር ካትሪን  በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እና በሆስፒታሎች አስፈላጊውን ህክምና ሲከታተሉ እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ1951 ዓ.ም ልዕልት ፀሐይ መታሰቢያ ሆስፒታል በአሁኑ ጦር ሀይሎች አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአዋላጅ ነርሶች ትምህርት ቤት ለማቋቋም ለሦስት ዓመት ኮንትራት አሁን በህይወት ከሌሉት ከባለቤታቸው ዶ/ር ሬጅናልድ ሐምሊንና ከ6 ዓመት ልጃቸው ጋር  ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ዶ/ር ካትሪን የወሊድ ጉዳት የሆነውን ፊስቱላ ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል ተቋም በመገባት ከ70,000 በላይ የአገራችን እናቶችና  ወጣት ሴቶች እክምናውን በነፃ አግኝተው ወደ ቀደመው ህይወታቸው እንዲመለሱ አስችለዋል፡፡

በትውልድ  አውስትራሊያዊ የሆኑት ዶ/ር ካትሪን  በበጎ አድራጎት ስራቸው  ከቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴ የክብር ሽልማት፣  ከቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያዊ ዜግነት የተበረከተላቸው ሲሆን በቅርቡ በድርጅታቸው 60ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከፍተኛ የኢትዮጰያ መንግስት የክብር ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ዓለም አቀፍ እውቅናዎችና ሽልማቶች የተበረከተላቸው ሲሆን ሁለት ጊዜ ለኖቤል ሽልማት እጩ ሆነውም ቀርበዋል፡፡

በዶ/ር ካትሪን እና በባለቤታቸው ዶ/ር ሬጅናልድ ሐምሊን በ1966 ዓ. ም የተቋቋመው ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ   በአሁኑ ወቅት  የአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታልን ጨምሮ በአገሪቱ አራቱም አቅጣጫዎች አምስት የህክምና ማዕከላትን፣  የሐምሊን ሚድዋይፎች ማሰልጠኛ ኮሌጅን እንዲሁም የተጎጂዎች ማገገሚያና መልሶ ማቋቋምያ ማዕከል አካቶ የሚያስተዳድር  ሲሆን በዓለማችንም ቀዳሚ ትኩረቱን ፊስቱላ ማከምና መከላከል ላይ አድርጎ እየሰራ የሚገኝ ብቸኛ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡

በዶ/ር ካትሪን ዕልፈት ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው፣ ለአጋሮቻቸውና ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናቱን እየተመኘን ስርዓተ-ቀብራቸውን በተመለከተ ዝርዝሩ ወደፊት እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ዶ/ር ካትሪን የአንድ ልጅ እና የአራት ልጅ ልጆች እናት እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

More News ተጨማሪ ዜና


    ሐምሊን ዜና መጽሔት

    እንግሊዝኛ Volume 4, Issue 2, August 2020 Volume 3, Issue 2, December 2019 Volume 3, Issue 1, April 2019 Volume 2, Issue 4, August 2018 Volume 2, Issue 3, May 2018 Volume 2, Issue 2, February 2018 Volume 2, Issue 1, November 2017 Volume 1, Issue 4, August 2017 Volume 1, Issue 3, May 2017 Volume 1. […]...

    ሐምሌ 1st, 2022 Read More ተጨማሪ

    ተጽዕኖ ሪፖርት FY22 – የሕክምና ፕሮግራም

    “አንዲት ልጅ ከአስከፊ ድህነት እና ሀዘን እና ሀዘን በድንገት አዲስ ሰው ስትሆን ለማየት የፊስቱላ ቀዶ ሐኪሞች ሲፈውሷቸው የሚያገኙት ደስታ ነው። – ዶክተር ካትሪን ሃምሊን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ከ10 ሴቶች መካከል 5 ያህሉ ያለ የህክምና እርዳታ በሚወልዱበት ፣ የተዘጋ ምጥ ለቀናት ሊቆይ እና የማህፀን ፌስቱላ ጉዳት ያስከትላል ።  የፊስቱላ አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ተፅእኖዎች በጣም አሳዛኝ ናቸው, ነገር ግን አብዛኛዎቹ […]...

    ሐምሌ 1st, 2022 Read More ተጨማሪ

    ተጽዕኖ ሪፖርት FY22 – የመልሶ ማቋቋም እና የመዋሃድ ፕሮግራም

    “በፊኛ ውስጥ ያለውን ቀዳዳ ብቻ የምናስተናግደው አይደለም፣ ሁሉንም በሽተኛ በፍቅር እና ርህራሄ እንይዛለን፣ ማንበብና መጻፍ እና የቁጥር ትምህርት፣ አዲስ ልብስ እና ወደ ቤት ለመጓዝ።” – ዶክተር ካትሪን ሃምሊን የሴት የማህፀን ፌስቱላ ጉዳት መጠገን የታሪኳ መጨረሻ አይደለም። ለወራት አልፎ ተርፎም ለዓመታት በማህበራዊ ተገልለው መኖር፣ ወደ ማህበረሰቡ እንደገና መግባት ከባድ ሊሆን ይችላል እና ጥቂት ሴቶች ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ […]...

    ሐምሌ 1st, 2022 Read More ተጨማሪ