ሀምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ

Support Hamlin Fistula Ethiopia today

Donate

ዛሬውኑ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ያግዙ

ይለግሱ
Visit the Hamlin Partner in your country
በእርስዎ ሐገር የሚገኝ የሐምሊን አጋር ይጎብኙ

“ሕልሜ የማሕፀን ፊስቱላን ከኢትዮጵያ ማጥፋት ነው። በሕይወት ዘመኔ ይሄን አላሳካ ይሆናል። እናንተ ግን ትችላላችሁ።

– ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን 

ከ63 ዓመታት በፊት በአውስትራሊያዊቷ ፋና ወጊ የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶክተር ካትሪን ሃምሊን እና ባለቤቷ ዶ/ር ሬግ ሃምሊን የተመሠረተው ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ እጅግ አሰቃቂ የሆነው የወሊድ ጉዳት ወይም የማሕፀን ፊስቱላ የደረሰባቸውን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለማከም ቁርጠኛ አቋም አለው።

ዛሬ ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የሃምሊን አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል፣ አምስት ክልላዊ ሃምሊን የፊስቱላ ሆስፒታሎችሃምሊን የአዋላጆች ኮሌጅ፣ ከ90 በላይ በሃምሊን የሚደገፉ አዋላጅ ክሊኒኮች እና የሃምሊን ማገገሚያ እና መልሶ ማቋቋም ማዕከልን (ደስታ መንደር) ያካትታል።

ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የማሕፀን ፊስቱላን በዓለም ዙሪያ ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ዋቢ ድርጅት እና መሪ ሆኖ ሴቶችን ሰብአዊነታቸውን እንዲያረጋግጡ፣ ጤናቸውን እና ደኅንነታቸውን እንዲያስጠብቁ እና በቤተሰባቸው እና ማኅበረሰባቸው ውስጥ የነበራቸውን ሚና መልሰው እንዲያገኙ የሚያስችል ሁለንተናዊ የሕክምና እና እንክብካቤ መንገድ በመፍጠር ፋና ወጊ ነው።

የማሕፀንፊስቱላአሳዛኝሁኔታእናየሃምሊንተስፋ

በሴቶች ላይ ሊደርሱ ከሚችሉ አስከፊ ነገሮች መካከል አንዱ የማሕፀን ፊስቱላ ወይም በምጥ መስተጓጎል ምክንያት የሚደርስ የውስጥ ጉዳት ሲሆን ሴቷ እራሷን እንዳትቆጣጠር ብሎም በማኅበረሰቧ የተገለለች እንድትሆን የሚያደርግ ነው።

የሃምሊን ቡድን የትኛዋም ሴት በማሕፀን ፊስቱላ ክብሯ መጎዳት እንደሌለባት ያምናል። የዶክተር ካትሪን ሃምሊን ሕልም ፊስቱላን ለዘላለም ማጥፋት ነበር – እና በእርስዎ ድጋፍ ሕልማቸውን ዕውን ለማድረግ እየተቃረብን ነው።

ከፊስቱላ ስቃይ ወደ ብሩህ ተስፋ የሚለውን የውባንቺን ታሪክ ከታች ይመልከቱ።

ሦስቱ ፕሮግራሞቻችን


የሕክምና ፕሮግራም

ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከአሰቃቂ እና መከላከል ከሚቻል የወሊድ ጉዳት ወይም የማሕፀን ፊስቱላ የተረፉ ሴቶችን ጤና እና ክብር ለማረጋገጥ የቆመ ነው።

ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፊስቱላ ሕክምና ቴክኒኩ የታወቀ ነው። በዶክተር ካትሪን ሃምሊን የተገነባው ይህ ፈር ቀዳጅ የቀዶ ጥገና ዘዴ በዓለም  ጤና ውስጥ እንደ ምርጥ ተሞክሮ ዕውቅና አግኝቷል።

አብዛኛውን ጊዜ ፊስቱላ በአንድ ሕይወትን በሚቀይር ቀዶ ጥገና ሊድን ይችላል። ይህም ለአንዳንዶች ከሁለት ሰዓት ያልበለጠ ጊዜ ብቻ ሊወስድ ይችላል።

የማገገሚያ እና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም

ሀምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ባለፉት 63 አመታት ከ70,000 በላይ የሚሆኑ ለማሕፀን ፊስቱላ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ጤና እና ክብር መልሷል። ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን የፊስቱላ ታካሚን ማከም በፊኛ ላይ ያለውን ቀዳዳ ማከም ብቻ ሳይሆን ሴትን በሙሉ በፍቅር እና በጥንቃቄ ማከም እንደሆነ ሁልጊዜ ያምኑ ነበር።

ለዚህም ነው በሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከፊስቱላ ጉዳት የሚያገግሙ ሴቶችን የበለጠ ለመደገፍ የማገገሚያ እና የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ያዘጋጁት። ፕሮግራሙ የሃምሊን የሕክምና ሞዴል ያቀፈ እና ሴቶች በነጻነት እና በክብር ሕይወታቸውን እንዲመሩ የሚያስችል ነው።

የመከላከል ፐሮግራም

የሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የማሕፀን ፊስቱላን ለማጥፋት ያለውን ራዕይ ለማሳካት በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ተጨማሪ አዋላጆች ያስፈልጉናል። አዋላጆች የእርግዝና ችግሮችን በመለየት የፊስቱላ ጉዳቶችን አስቀድመው መከላከል ይችላሉ።

ለዚህም ነው እ.አ.አ. በ2007 ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን በመላው ኢትዮጵያ ለማሳደግ የሃምሊን አዋላጆች ኮሌጅን ያቋቋሙት። የሃምሊን አዋላጆች ኮሌጅ በኢትዮጵያ የአዋላጆች ሥልጠና የልህቀት ማዕከል ነው።

የክሊኒካል እና የፕሮግራም ቡድናችንን ያግኙ


የሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ቡድን 100% በኢትዮጵያዊያን የተዋቀረ ሲሆን ወደ 600 የሚጠጉ ባለሙያዎች አሉት። ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ በዶክተር ካትሪን ሃምሊን የሠለጠኑ ሲሆን በሃምሊን የሕክምና ሞዴል በማሕፀን ፊስቱላ የተጎዱ ሴቶችን ለማከም በድርጅቱ ውስጥ ይሰራሉ፤ የካትሪንን እና የሬግን ራዕይ እና ስራንም አስቀጥለዋል። የእኛን የሕክምና፣ የማገገሚ እና የመልሶ ማቋቋም፣ እንዲሁም የመከላከል ቡድን አባላትን ለማግኘት ከዚህ በታች ጠቅ ያድርጉ።

የሃምሊንፊስቱላኢትዮጵያን ወቅታዊመረጃዎችንእናታሪኮችንያንብቡ


‘Hamlin Midwives Alumni Network’ Summit Kicks off

The Hamlin College of Midwives and GreenLamp collaboratively launched the “Hamlin Midwives Alumni Network” on July 28, 2018 at Elilly International Hotel, Addis Ababa. The summit was attended by more than 80 graduates of the Hamlin College of Midwives, representatives of GreenLamp, academic staff of Hamlin College of Midwives and …

HCM Celebrates 8th Class Graduation and 10th Anniversary

The Hamlin College of Midwives (HCM) celebrated its 8th Class graduation and 10th anniversary on July 14, 2018 at  Defence Force Officers Club’s compound,  Addis Abeba.    This year the college graduated 20 midwives with BSc Degree in Midwifery, raising the total number of Hamlin midwives to 145 since 2007, the …

H.E the First Lady of Ethiopia Visits the Addis Ababa Fistula Hospital

H.E the First Lady of Ethiopia, W/ro Zinash Tayachew, together with H.E Minister of the Federal Ministry of Health, Dr. Amir Aman, visited the Addis Ababa Fistula Hospital on May 31, 2018. During their visit, they were most cordially welcomed by Dr. Catherine Hamlin, Hamlin Board of Trustees, Senior Management …