ሃምሊን ሕክምና ሞዴል

“እኛየምናክመውበፊኛውስጥያለውንቱቦብቻአይደለም፣ሁሉንምታካሚፍቅርእናክብካቤበመስጠት፣በማስተማር፣በጥበብበማበልፀግ፣አዳዲስልብሶችንአልብሰንእናወደቤታቸውመመለሻገንዘብሰጥተንነውየምንሸኘው።” 

– ዶክተር ካትሪን ሃምሊን

የሃምሊንሕክምናሞዴልምንድንነው?


የማሕፀን ፊስቱላ ተፅዕኖ ከአካላዊ ጉዳቶች በላይ የረቀቀ ነው። ብዙውን ጊዜ ልጅን በሞት ማጣት፣ የመገለል እና የኀፍረት ስሜት እንዲከሰት ያደርጋል።


ላለፉት 60 ዓመታት በላይ ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ጊዜ በሚገጥም የማሕፀን ፊስቱላ ሕሙማንን ለማከም እና ለመንከባከብ ሁሉን አቀፍ አሠራር ሲተገበር ቆይቷል – ‘የሃምሊን ሕክምና ሞዴል’። በፊት የፊስቱላ ሕመምተኞች የነበሩ ሴቶችን ከቀዶ ሕክምና በኋላ ቶሎ እንዲያገግሙ እና  ሁሉም ጤናማ የመሆን ዕድል እንዲኖራቸው የሚያደርግ የተረጋገጠ ዘዴ ነው። ይህ የሃምሊን ሕክምና ሞዴል የማሕፀን ፊስቱላን ማከምን ጨምሮ በወሊድ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን፣ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶችን ለማከም ይጠቅማል።
ዶክተር ካትሪን ሃምሊን የበለፀገው  የሃምሊን ሕክምና ሞዴል ለታካሚዎች መሠረታዊ አክብሮት፣ የተሟላ እና ርህራሄ የተሞላበት እንክብካቤ አገልግሎት በመስጠት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ ሞዴል በዓለም ላይ በማስፋፋት ላይ ነው።

https://youtu.be/fARZbM9Ent4

የሃምሊንየሕክምናሞዴልየሚከተሉትንያጠቃልላል:


የታካሚዎች መለያ

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብዙ የማሕፀን ፊስቱላ ተጠቂ ሴቶች እርዳታ ማግኘት እንደሚችሉ እንኳ አያውቁም። ልዩ የሆነው የሃምሊን የሕሙማን ልየታ ፕሮግራም እነዚህን ሴቶችን ለማግኘት እና ለማዳን  በመገናኛ ብዙኃን ዘመቻዎችን በማድረግ  እና ቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ፣ ማኅበረሰቡን በማስተማር እንዲሁም የተለዩ ሕሙማንን ከስድስቱ የሃምሊን ሆስፒታሎች በአንዱ መሠረታዊ ሕክምና እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።

የቀዶ ሕክምና

አንዲት የሁለት ሰዓት ቀዶ ሕክምና ሥራ የፊስቱላ ጉዳትን በመጠገን የሴትን ሕይወት ሊያተርፍ ይችላል። ነገር ግን ለብዙ ዓመታት ሲሰቃዩ የነበሩ ሴቶች እንደ ጠባሳ ቲሹ፣ በረዥም ጊዜ የሚፈጠር ተህዋሲያን እንዲሁም የኩላሊት መጎዳትና በመሳሰሉ ውስብስብ ችግሮች ስለሚጠቁ የበለጠ ውስብስብ ቀዶ ሕክምና እና ማገገሚያ እንክብካቤ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። የሃምሊን የሐኪሞች ቡድን አሠራር እና የቀዶ ሕክምና ቴክኒክ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ በጣም ተመራጭ የፊስቱላ ሕክምና ዘዴ ተደርጎ እየተወሰደ ነው። 

አለባበስእናየሃምሊንብርድልብስ

የሴቷ መፈወስ የሚጀምረው ገና ሃምሊን ሆስፒታል እንደደረሰች ነው. ሕይወቷን አንድ ላይ እንደተሳሰረ የሚያሳይ በብዙ ቀለማት ያሸበረቀ በእጅ የተሠራ ብርድ ልብስ ትቀበላለች። በቆይታ ጊዜዋ የምትለብሰው የሌሊት ልብስና ነጠላ ጫማ ይበረከትላታል። ሆስፒታሉን ለቃ በማትወጣበት ጊዜ ደግሞ ወደ ቤቷ የምትመለስበትንና ቀን ለማክበር አዲስ ልብስ ይሰጣታል።

የተመጣጠነምግብ

ጥሩ አመጋገብ አስፈላጊ እና የሕክምና አካል ነው። ፊስቱላ ያጋጠማቸው ብዙ ሴቶች ሕይወታቸውን ሙሉ ከሰው ተደብቀውና ተነጥለው ስለሚኖሩ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያጋጥማቸዋል። በሃምሊን ሆስፒታሎች ውስጥ የሚቆዩ ሕሙማን በቆይታ ጊዜያቸው በሙሉ ጤናማ እና የተመጣጠነ ምግብ ይሰጣቸዋል፤ የቀድሞ ጥንካሬያቸውን እና ብርታታቸውንም መልሰው ያገኛሉ።

 ፊዚዮትራፒ (አካላዊሕክምና)

ከባድ የሆነ የአካል እንግልት የነርቭ ጉዳት ሊያደርስ ይይችላል፤ ለረጅም ጊዜ አለመንቀሳቀስ ደግሞ የጡንቻ መኮማተርን ያስከትላል። አብዛኛዎቹ የፊስቱላ ጉዳት ያጋጠማቸው ሴቶች መሰል ችግር ያጋጥማቸዋል። ሁሉም የሃምሊን ታካሚዎች ወደ ቀዶ ሕክምና ከመግባታቸው በፊት እና ከወጡ በኋላ ጡንቻዎቻቸው ሙሉ በሙሉ  መሥራታቸውን ለማረጋገጥ ሲባል በተዘጋጀው የፊዚዮቴራፒ ፕሮግራም  አገልግሎት ያገኛሉ። 

የሴቶችድጋፍፕሮግራም

የሃምሊን የሴቶች ድጋፍ ፕሮግራም በደስታ መንደር (በሃምሊን የማገገሚያ እና መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል) ውስጥ ለሚገኙ እና የገንዘብ ድጋፍ ለሚሹ የፊስቱላ ሕሙማን የክኅሎት ሥልጠና ይሰጣል። በየዓመቱ ከ 200 በላይ የሚሆኑ ሴቶች በዚህ መሠረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መርሐ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋሉ፤ የተለያዩ ዕድሎችን ማለትም  የአመራር እና የተግባቦት ሥልጠናዎችን እና የአነስተኛ ንግድ አሠራር ሥልጠናዎችን ያገኛሉ። እነዚህ ሕይወትን ቅያሪ እሴቶች ሴቶች የራሳቸው ምርጫ  እንዲኖራቸው እና ራሳቸውን የመቻል አቅም እንዲኖራቸው ፍላጎታቸውን እንዲያነሣሡ ያግዟቸዋል። የበለጠ ለማወቅ ይህንን ይጫኑ (እባክዎን ወሂቡን ከWEP ክፍል በ  «R&R» ያገናኙ)

የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ

ብዙ ሴቶች ባጋጠማቸው አስከፊ የፊስቱላ ጉዳት ምክንያት ሙሉ ሕይወታቸው ምስቅልቅል ብሎባቸዋል። ብዙ ጊዜም ከማኅበረሰቡ ይገለላሉ። ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ሴቶችን ወደ ማኅበረሰባቸው እንዲቀላቀሉ እና ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ ለማድረግ ዘላቂ የሆነ ሥራ እስኪያገኙ ወይም የራሳቸውን ንግድ እስከሚጀምሩ ድረስ ድጋፍ ይሰጣቸዋል። ይህ ድጋፍ ሴቶች ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ለመርዳት ወሳኝነት አለው።

የሙያ ክኅሎት ሥልጠና

የሃምሊን ሕክምና ሞዴል ሴቶች ሕይወታቸውን እንዲመሩ ለማብቃት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል። ሕሙማን ሴቶች በሃምሊን ሆስፒታል በሚቆዩበት ጊዜ ንቃተ ኅሊናቸውን ለማሳደግ እና የትምህርት ክኅሎታቸውን በማዳበር ለሦስት ወራት ያህል የሙያ እና የሕይወት ክኅሎት ሥልጠና እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን በራስ የመተማመን አቅማቸውን በማሳደግ ወደ ማኅበረሰባቸው እንዲመለሱ እና ገቢ ማግኘት እንዲችሉ ይደረጋሉ።

 የምክር አገልግሎት

በፊስቱላ ምክንያት የሚገጥም የሥነ ልቦና ጉዳት አብዛኛውን ጊዜ ከአካላዊ ጉዳት የበለጠ ጠባሳ ጥሎ ሊያልፍ ይችላል። የሥነ ልቦና ጉዳትን መጠገን እና በራስ የመተማመንን አቅም ማዳበር የመልሶ ማቋቋም ሥራ ቁልፍ ተግባር ነው።  ለዓመታት በኀፍረት ተሸብበውእና ተገልለው የኖሩ ሴቶች ወደ ቀድሞው የራሳቸው ስሜት እንዲመለሱ ለማድረግ ሲባል ቅንነት የተሞላበት ድጋፍ ያገኛሉ።