የሕክምናእናፕሮግራምቡድን

የሕክምና ቡድን አባላት 


ዶክተርየሺነህደምረው

በሃምሊንፊስቱላ-ኢትዮጵያሜዲካልዳይሬክተርናየቀዶ ሐኪም

ዶ/ር የሺነህ በሃምሊን አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል እና በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ  በሚገኙ አምስት የክልል የፊስቱላ ሆስፒታሎች ውስጥ ያለውን ሕክምና አሰጣጥ (ክሊኒካዊ አተገባበርን) ይቆጣጠራሉ።በተጨማሪም ከዓለም አቀፉ የማሕፀንና የፅንስ ሕክምና ፌዴሬሽን በፊስቱላ ቀዶ ሕክምና አሠልጣኝነት ዕውቅና አግኝተዋል።   ከጎንደር ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ከተመረቁ በኋላ በጠቅላላ ሐኪምነት እ.ኤ.አ. 1987 ሥራቸውን ጀምረዋል።  እ.ኤ.አ. በ 1997 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፅንስና ማሕፀን ሕክምና ስፔሻሊስትነት ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 2019 በመቀሌ ዩኒቨርስቲ በዩሮጋይናኮሎጂ ሲኒየር ፌሎዉሺፕ ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።  ባለፉት 23 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ከሚታወቁት የፅንስና ማሕፀን ሐኪሞች መካከል አንዱ ናቸው። ለ 17 ዓመታት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች እና ለሦስት ዓመታት ደግሞ በሃምሊን መቱ ፊስቱላ ሆስፒታል ውስጥ አገልግለዋል።

Sister Tirgalem

ሲስተር ትርጋለም

በሃምሊን አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ውስጥ ማትሮን 

ሲስተር ትርጋለም በየነ በሃምሊን አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ተጠባባቂ ማትሮን ናቸው። እ.ኤ.አ. ከሰኔ 16/ 2008 ጀምሮ በሃምሊን ፊስቱላ-ኢትዮጵያ ውስጥ እየሠሩ ይገኛሉ። ሲስተር ትርጋለም ወደ ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ ይሠሩ ነበር።

ትርጋለም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ጳውሎስ ነርሲንግ ትምህርት ቤት በነርስነት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።  ትርጋለም ኢትዮጵያ ከፊስቱላ፣ ከእናቶች እና ከጨቅላ ሞት ነጻ ሆና ማየት እና ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሴቶች በሠለጠነ የማዋለድ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነው በሰላም ሲወልዱ ማየት ይፈልጋሉ።

ማሚቱጋሸ 

በሃምሊንአዲስአበባፊስቱላሆስፒታልየቀዶ ሐኪም 

ማሚቱ ጋሸ በሃምሊን ፊስቱላ-ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት የፊስቱላ የቀዶ ሐኪም በመሆን አገልግለዋል። ራሳቸው ታካሚ የነበሩት ማሚቱ የፊስቱላ ቀዶ ጥገና ሕክምናን የተማሩት ከዶክተር ካትሪን እና ዶክተር ሬጅ ሃምሊን ነው። ማሚቱ እ.ኤ.አ. በ1989 ከዶክተር ሬጅ እና ዶክተር ካትሪን ሃምሊን ጋር በመሆን ለንደን ከሚገኘው ሮያል የቀዶ ሕክምና ኮሌጅ በቀዶ ሕክምና ዘርፍ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልመዋል።  እ.ኤ.አ. በ2000 በወሊድ ጊዜ የሚከሰትን ፊስቱላ ለማከም የሚረዳውን የሃምሊን ሕክምና ሞዴል በዓለም ዙሪያ ለማስፋፋት ወደ ተለያዩ አገሮች ተጉዘዋል።  በአሁኑ ወቅት ማሚቱ በሃምሊን አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ውስጥ ከሌሎች የቀዶ ሐኪሞች ጋር ተባብረው  መሥራታቸውን ቀጥለዋል።

ዶክተር ቢዴ ለማ 

በሃምሊን አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል የቀዶ ሐኪም

ዶ/ር ቢዴ ለማ ዩሮሎጂስት እና የኢትዮጵያ የዩሮሎጂስት ማኅበር ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ቀደም ሲል ደግሞ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና ሐኪም ነበሩ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  የቀዶ ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ እና ፕሮፌሰር በመሆንም አገልግለዋል።

ዶ/ር መላኩ አብርሃ

በሃምሊንመቀሌፊስቱላሆስፒታልየሕክምናዳይሬክተርእናየቀዶ ሐኪም 

ዶ/ር መላኩ አብርሃ ለ30 ዓመታት ያህል  የሕክምና ልምድ ያላቸው ከፍተኛ የፅንስና የማሕፀን ሐኪም እና ዩሮጋይናኮሎሮጂስት ናቸው። ዶ/ር መላኩ ላለፉት 16 ዓመታት የሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የሕክምና ቡድን አባል ሆነው በመሆን አገልግለዋል። እ.ኤ.አ. በ 2017  ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ፌሎዉሺፕ ፕሮግራም ተከታትለዋል። አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኘው የሃምሊን መቀሌ ፊስቱላ ሆስፒታል ኃላፊ ናቸው።

ዶ/ርቢኒያምሲራክ

በሃምሊን ይርጋለም ፊስቱላ ሆስፒታል የሕክምና ዳይሬክተር እና የቀዶ ሐኪም 

ዶ/ር ቢኒያም ሲራክ ላለፉት 15 ዓመታት በማሕፀን፣ ፅንስ እና ዩሮጋይናኮሎጂ  ሐኪምነት ሠርተዋል። ያላቸውን የዳበረ የማሕፀን ሕክምና ሙያ ዕውቀት በመጠቀም ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን ሌሎች ባለሙያዎችን አስተምረዋል። እኚህ ታታሪ የሕክምና ባለሙያ  ከሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ለእናቶች ክብካቤ ከፍተኛ ልምዳቸውን ተጠቅመው እስከ መጨረሻው ለመሥራት ወስነዋል። በአሁኑ ጊዜ የዩሮጋይናኮሎጂ የመጨረሻ ዓመት ፌሎሽፕ ትምህርት ተከታታይ ናቸው።

ዶክተር ወንዱ በላይነህ

በሃምሊን ይርጋለም ፊስቱላ ሆስፒታል የቀዶ ሐኪም 

ዶ/ር ወንዱ በላይነህ ዴጊና በሃምሊን ይርጋለም ፊስቱላ ሆስፒታል የፊስቱላ ቀዶ ጥገና ሐኪም ሲሆኑ በሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ውስጥ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 2022 ጀምሮ በመሥራት ላይ ናቸው።  ከዚህ በፊት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የሠሩ ሲሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ነበሩ። ትምህርታቸውን የተከታተሉት ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ነው።  ዶ/ር ወንዱ  ልዩ ሙያውን (ስፔሻሊቲ) ለማጠናቀቅ እና ተጨማሪ የምርምር ሥራዎችን ለመሥራት በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

ዶ/ር ቢተው አበበ

አበበ በሃምሊን ባሕር ዳር ፊስቱላ ሆስፒታል የሕክምና ዳይሬክተር 

ዶክተር ቢተው አበበ በሃምሊን ባሕር ዳር ፊስቱላ ሆስፒታል የሕክምና ዳይሬክተር ናቸው። ዶ/ር ቢተው እ.አ.አ. በ 2009 ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን በመቀላቀል የፊስቱላ ቀዶ ጥገና ሐኪም እና ዩሮጋይናኮሎጂስት ሆነው እየሠሩ ነው። ወደ ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ሳይንስ የተማሩ ሲሆን በፅንስና ማሕፀን ሕክምና ስፔሻሊስትነት ማዕረግ አግኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ አገልግለዋል። እ.ኤ.አ. በ 2019 በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዩሮጋይናኮሎጂ ከፍተኛ ፌሎሺፕ ፕሮግራም ትምህርትን አጠናቀዋል።

ዶክተርለታገደፋአራርሳ

በሃምሊን ሀረር ፊስቱላ ሆስፒታል የሕክምና ዳይሬክተር እና የቀዶ ሐኪም 

በዶክተር ሬጅ እና በዶክተር ካትሪን ሀምሊን ለሥራ የተነሣሡት ዶ/ር ለታ እ.አ.አ. ሴፕቴምበር 2020 በሃምሊን ሀረር ፊስቱላ ሆስፒታል የፊስቱላ ቀዶ ጥገና ሐኪም ሆነው መሥራት ጀመሩ። ዶ/ር ለታ በአሁኑ ጊዜ ጾታ ተኮር ጥቃት፣ በማሕፀን እና መፀዳጃ አካላት ጉዳት እና የሴት ልጅ ግርዛትን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ ናቸው። ዶ/ር ለታ ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ከመቀላቀላቸው በፊት በጀጎል ሆስፒታል እና በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ሠርተዋል። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተማሩ ሲሆን በጀርመን የሕክምና ቡድን አባላት አማካኝነት በወሊድ ጊዜ ስለሚከሰት ፊስቱላ፣ እንዲሁም በወሊድና መፀዳጃ አካላት ጉዳት ዙሪያ ሥልጠናዎችን ወስደዋል።

ዶ/ር ዘሃራ ሷሊህ

በሃምሊን መቱ ፊስቱላ ሆስፒታል የሕክምና ዳይሬክተር እና የቀዶ ሐኪም 

ዶ/ር ዘሃራ ሷሊህ በሃምሊን መቱ ፊስቱላ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሐኪም እና ዩሮጋይናኮሎጂስት ናቸው። እኚህ ኦብስትሪሺያን ጋይናኮሎጂስት በሃምሊን የሐኪሞች ቡድን ውስጥ እጅግ የተከበሩ ሐኪም ናቸው።  ዶ/ር ዘሃራ በመቱ ካርል ሆስፒታል ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 2015 ጀምሮ ሃምሊን ፊስቱላ-ኢትዮጵያን ተቀላቀሉ። የፅንስና ማሕፀን ሕክምናን በማጥናት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል።

የቅድመ መከላከል  ቡድን 


ወይዘሮ ቆንጂት ካሳሁን

በሃምሊንየአዋላጅነርሶችኮሌጅዲንእናእናየቅድመመከላከልሥራአስኪያጅ

ወይዘሮ ቆንጂት እ.ኤ.አ. በ 2021 በሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በሃገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ መከላከል ስትራቴጂ ኃላፊነትን ወስደው የሃምሊን ሚድዋይቭስ (አዋላጆች) ኮሌጅ ዲን ሆኖው ተሾሙ። ወ/ሮ ቆንጂት እ.ኤ.አ. በ2005 ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን በመቀላቀል በተለያዩ የሕክምና ኃላፊነቶች ሥር የሠሩ ሲሆን ለአራት ዓመታት ያህልም የሃምሊን አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ማትሮን በመሆንም ሠርተዋል። ወይዘሮ ቆንጂት በነርሲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በማኅበራዊ ሳይኮሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ወ/ሮ ቆንጂት በዘርፉ ለሚማሩ ተማሪዎችም ሆነ ተመራቂዎች ጥሩ አርአያ ሲሆኑ  የቅድመ መከላከል ፕሮግራምን ለማስፋፋት እና ሁሉም የሃምሊን አዋላጆችን ለመረዳት ጠቃሚ ድጋፍ በመስጠት እየሠሩ ነው።

ሲስተር ማሪት 

የሃምሊን ሚድዋይቭስ ኮሌጅ ምክትል ዲን

ሲስተር ማሪት እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ በሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ተቀላቅለው እየሠሩ ነው።  ሲስተር ሜሪት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአዋላጅነት የመጀመሪያ ዲግሪ እና በአጠቃላይ ነርስነት ደግሞ ዲፕሎማ ያላቸው ሲሆን ከአልፋ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በሥራ አመራር የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው። ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም በእናቶች ጤና እና ሥነ ተዋልዶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ሲስተር ማሪት ሃምሊን ፊስቱላ-ኢትዮጵያን ከመቀላቀላቸው በፊት ለስድስት ዓመታት ያህል  በነርስነት ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ በተለያዩ የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ለ13 ዓመታት ያህል በአዋላጅነት ሠርተዋል። ሲስተር ማሪት  በሃምሊን ሚድዋይቭስ ኮሌጅ ውስጥ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲኖር በማስተባበር፣ በማቀድ፣ እና በመቆጣጠር ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።

የመልሶማቋቋምቡድን


ወይዘሮ ትግሥት አማን

የመልሶ ማቋቋም እና ማገገም ሥራ አስኪያጅ

ወይዘሮ ትግስት በትምህርት ዕቅድና ሥራ አመራር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ሰብአዊነት ላይ በሚሠሩ ተቋማት ላይ የ24 ዓመት የሥራ ልምድ አላቸው። እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ በሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የጎልማሶች እና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አስተባባሪ ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል።  የመልሶ ማቋቋም እና ማገገሚያ ሥራ አስኪያጅ በመሆንም በሠሩት ሥራ  ሕሙማን ስለራሳቸው ያላቸውን ግምት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያሳድጉ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ እና ድህነትን በማሸነፍ ራሳቸውን እንዲችሉ በመርዳት እና በማበረታታት ላይ ይገኛሉ። ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ከመቀላቀላቸው በፊት በተለያዩ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከቅድመ ትምህርት እስከ ኮሌጅ ድረስ በመምህርነት አገልግለዋል።