«ሁሉም ለኔ የተወደዱ እና ዋጋ የምሰጣቸው ናቸው። ወደእኛ ለምትመጣ እያንዳንዷ ታካሚ፤ ፍቅር እና ክብካቤ እንሰጣለን፤ እንዲሁም ወደ ተሻለ እና መደበኛ ሕይወት እንዲመለሱ አስፈላጊውን ልምድ እናካፍላለን»
– ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን
መልሶ በማቋቋምጤና እና ክብርን መመለስ
ባለፉት 63 ዓመታት በኢትዮጵያ የሃምሊን ፊስቱላ ማዕከል በወሊድ ምክንያት የተፈጠረ ፊስቱላ ያለባቸው ከ70,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ጤና እና ክብር ወደነበረበት መልሷል። ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ፊስቱላ ያለባቸውን ማከም ማለት በፊኛ የሚገኘውን ሸንቁር መጠገን ብቻ ሳይሆን፤ ሴቷን በፍቅር እና ክብካቤ መያዝ እንደሆነ ሁሌም ያምኑ ነበር።
በኢትዮጵያ የሃምሊን ፊስቱላ ማዕከል የመልሶ ማቋቋም እና መቀላቀል መርሐግብርን ቀርጻ ያስጀመረችውም በዚህ እምነት በመመርኮዝ ከፊስቱላ ጉዳት እያገገሙ ያሉ ሴቶችን በቀጣይነት ለመደገፍ ነው። መርሐግብሩ የሃምሊን የጤና ክብካቤ ሞዴልን በሥራ ላይ የሚያውል እና ሴቶች ሕይወታቸውን ራሳቸውን ችለው በክብር እንዲኖሩት የሚያበቃ ነው።
የቅርብ ጊዜ የተፅዕኖ ሪፖርታችንን ለማንበብ ይህንን ማገናኛ (ሊንክ) ይጫኑ (እ.ኤ.አ. ለ2022 የበጀት ዓመት የተፅዕኖ ሪፖርት ማገናኛ (ሊንክ))
የሃምሊን መልሶ ማቋቋም እና መቀላቀል ማዕከል – ደስታ መንደር
እ.ኤ.አ. 2002 ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን የመልሶ ማቋቋም እና መቀላቀል ማዕከል የሆነውን ደስታ መንደር መሠረቱ። መንደሩ የፊስቱላ የጤና እክል ለረዥም ጊዜ የቆየባቸው እና የጉዳት መጠናቸው ከባድ የሆነ ታካሚዎች የሚያገግሙበት እና ማብቃት የሚያስፈልጋቸውን ደግሞ ሥልጠና እንዲሁም የሥነ ልቦና እና ማኅበረሰባዊ ድጋፍ ለማግኘት የሚቆዩበት ተቋም ነው። የጤና እክላቸው የተወሳሰበባቸው አንዳንድ ሴቶች ከአንድ በላይ ቀዶ ጥገና እና ቀጣይ የሆነ የጤና ክብካቤ ያስፈልጋቸዋል።
የአንዲትን ሴት የፊስቱላ ጉዳት መጠገን የታሪኳ መቋጫ አይደለም። ለረዥም ወራት፤ ከዛም አልፎ ለዓመታት ከማኅበረሰቡ ተገልላ በመቆየቷ፤ መልሾ ማኅበረሰቡን መከላከል ስጋት የሚጭር ይሆናል። ራሳቸውን ችለው ለመኖር የሚያስችላቸው የራሳቸው ገቢ ያላቸው ደግሞ ጥቂት ናቸው።
በደስታ መንደር እያንዳንዷ ሴት ለራሷ እንዲመጥን ተደርጎ የሚነደፍ የመልሶ ማቋቋም እና መቀላቀል መርሐግብር ዕቅድ ይኖራታል። ሴቶች የምክር አገልግሎት የፊደል እና የቁጥር/ሒሳብ/ ትምህርት እንዲሁም የሙያ እና የሕይወት ክኅሎት ሥልጠና ይሰጣቸዋል።
የሃምሊን ቡድን ሴቶች ወደነበረቡት ማኅበረሰብ መልሰው ሲቀላቀሉ፤ ዘላቂ ሥራ እንዲያገኙ ድጋፍ ይሰጣል። አንዳንድ ጊዜ ይህ ድጋፍ የራሳቸውን የንግድ ሥራ እንዲጀምሩ ወረት/ካፒታል/ የሚያገኙበትን መንገድ ማስተባበርንም ይጨምራል። ይህም ሴቶች የራሳቸውን ገቢ እንዲያመነጩ የሚያግዝ ነው።
የሃምሊን ሴቶችን የማብቃት መርሐግብር
እ.ኤ.አ በ2021 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሃምሊን ፊስቱላ ከዊመን ሆፕ ኢንተርናሽናል ድጋፍ በማግኘት ተጨማሪ ከፊስቱላ ያገገሙ ታካሚዎች በደስታ መንደር ትምህርት እንዲያገኙ ዕድል የሚሰጥ የሴቶች ማብቃት መርሐግብር ቀርጾ ሥራ አስጀምሯል። (ከላይ የቀለመው ዊመን ሆፕ ኢንተርናሽናልን የሚመለከት ጽሑፍ ወደሚኝበት የ ‘ፕሮግራም አጋሮች ‘ ገጽ የሚመራ ማገናኛ (ሊንክ) ነው)
ይህ ፈርቀዳጅ የሆነ ኢኒሺዬቲቭ ሴቶች አማራጭ እንዲኖራቸው እና ራሳቸውን ችለው ሕይወታቸውን እንዲኖሩ የሚያበቃ ነው። እነሱም በተራቸው ማኅበረሰባቸውን እና በአካባቢያቸው ያሉትን ሰዎች ማብቃት ይችላሉ። መርሐግብሩ የመሪነት እና ሥነተግባቦት ሥልጠና እና ስለ አነስተኛ ንግድ ሥራ መመሪያ መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ዕድሎችን የሚሰጥ ነው።
ትግሥት አማን፣ የሃምሊን የመልሶ ማቋቋም እና መቀላቀል ሥራ አስኪያጅ ስትሆን የሴቶች ማብቃት መርሐግብሩ በደስታ መንደር የሚሠራውን ሥራ የሚያግዝ እና የሚያሟላ እንደሆነ እምነት አላት።
«ተጨማሪ የሙያ ክኅሎት ሥልጠናው በወሊድ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችን የፈውስ/የመዳን/ ሂደት የተሟላ እንዲሆን የሚያደርግ እና በራስ መተማመን መንፈስ ኑሯቸውን መልሰው ለማስተካካል የሚየበቃቸው ነው» ብላለች።
ከቀድሞ ታካሚዎች የመጡት ግብረመልሶች እጅግ በአመዛኙ አዎንታዊ ናቸው። «መርሐ ግብሩ እንደ ሙሉ ላሉ ሴቶች የእውነት ሕይወታቸውን የሚቀይር ነው። በጣም በስቃይ ነበር የምኖረው። ከዳንኩ በኋላ ይህንን ሥልጠና እንድወስድ ስጋበዝ፤ በጣም ከመደሰቴ ብዛት የምለው ነገር ጠፍቶብኝ ነበር…በመንደሬ አነስተኛ የመኝታ አገልግሎት የሚሰጥ ምግብ ቤት የመክፈት ተስፋ አለኝ።»